S5 MP3 Player - плагин joomla Mp3

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ለዓለም ዓለም አሜን።
ላለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ የዚህ በኃይማኖት ሽፋን ቤተ-ክርስቲያንን የሚያውክ፤ ክርስትያኖችም የሚያሳድድ ጸረ-ወንጌል አሸባሪ ድርጅት በአማርኛ “ማኅበረ ቅዱሳን” በትግርኛ “ታማልዳለች” በመባል የሚታወቀው የሸማቂዎች ማኅበር (ሸማቂ፥ ማለት ጻድቅ መስሎ የሚያጠምድ ገዳይ

ማለት ነው ሉቃ. 20፥20 ይመልከቱ) ድንበር የለሽ የህውከት አገልግለቱ በስፋት በኤርትራ አብያተ-ክርስቲያናት የፈጸመው ወንጀልና እኩይ ምግባር ተመልክተናል ለዛሬ ደግሞ በአሁን ሰዓት በኤርትራ ምድር እንቅስቃሴው ምን ይመስላል? በየትኛው የሥራ መስክ ተሰማርቶስ ይገኛል? የሚሉትንና ሌሎች ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂ የሰይጣኑ ማኅበር “ማኅበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ በማያፈናፍን መልኩ ቁልጭ አድግርገው የሚያሳዩ መረጀዎችም ይዣለሁ መልካም ንባብ።

“ማኅበረ ቅዱሳን” በአሁን ሰዓት አስመራ ከተማ ስላለው እንቅስቃሴ እንዴት ልታውቅ ቻልክ? ለሚል ጥያቄ መልሴ “ሞኝ አንድ ጊዜ ስደበው ሺ ጊዜ ራሱን እየሰደበ ይኖራል” እንዳሉት አበው በተጨባጭ መረጃዎች የተደግፉ በጥራትና በብስለት የተጻፉ በማኅበሩ ዙርያ ላይ የሚያብጠነጥኑ ክፍል አንድና ክፍል ሁለት መጻህፍቶቼን ተከትሎ በመረጃ መልስ ከመስጠት ይልቅ የግል ህይወቴን በመፍተል በተባራሪ ልሳኖቹና አሜሪካ ከሚገኘው ሬድዮ ጣቢያ ከሚያሰማው የያዙኝ ልቀቁኝ ዘፈን  የተነሣ ያለ ክፍያ በሰራው ማስታወቂያ የተጻፉ መጻህፍት ከወትሮ በበለጠ መልኩ ተፈላጊነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመምጣቱ ዕድሜ ለቴክኖሎጂ አንባቢም በደረቅ ኮፒና በሶፍት ኮፒ እየተቀባበለ ክፍል አንድ መጽሐፌ አሥመራ ይገባል እላችኃለሁ።

በአሁን ሰዓት ክፍል አንድ መጽሐፌ አሥመራ ከተማ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የቅድስት ቤተ-ክርስትያን ልጆች በአድራሻዬ ባቀረቡልኝ ጥያቄ መሰረት ወደ ትግርኛ ለመለስ የትርጉም ሥራ አንደ ጀመሩና እንዲሁም ደግሞ ማኅበሩን በኤርትራ አብያተ ክርስቲያናት የፈጸመውን ቃላት የማይገልጸው ሰይጣናዊ ድርጊት በህግ ፊት ለማስቆም ድንበር የያዛዋቸው መልካምን ቀን የሚጠባበቁ የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት መምህራን እና አባቶች ከዚህ በፊት ያቀረብኳቸውና አሁንም የማቀርበው መረጃ በአድራሻ የላኩልኝ ሲሆን ስለ ወቅታዊ እንቅስቃሴውም ምን እንደሚመስልና በምን ዓይነት መልኩ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ በመጠኑ ጠቁመውኛል።

በመጀመሪያዎቹ አከባቢ እነዚህ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የተመለሱ ተውልደ ኤርትራውያን የ“ማኅበረ ቅዱሳን” አባላት የነበሩ ግለ ሰቦች በቤተ-ክርስትያን ከፈጠሩት ውዝግብ በተጨማሪ የኤርትራ ህዝብ በኢትዮጵያ ህዝብ ያለው አመለካከት የተበላሸ ምስል ይኖረው ዘንድም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል እንዲሁም ደግሞ ሀገራቸው እንዲገቡ የተደረጉ የኦርቶዶክስ አማኞች ከወገኖቻቸው በእምነት ከሚመስልዋቸው ኦርቶዶክሳውያን እጅ ለእጅ ተያይዘው ቤተ-ክርስቲያናቸውን በአንድነት እንዳይዙና አምላካቸውን እንዳያመልኩ በጎራ በመለየት ብዙሃኑ የዋሃን በማታለል ለበለጠ ሰይጣናዊ አገልግሎቱ እንደ አጋጣሚ ተጠቅመውበታል በአሁን ሰዓት በአሥመራ ከተማ እንቅስቃሴው ከዚህ አልፎ የይ ህ.ግ.ደ.ፍ መንግሥት በቤተ-እምነቶች ላይ የወሰደውን አረመንያዊ እርምጃ ጎን በመቆም ቀድሞ እንከን ያላገኘባቸው ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የሲ.አይ.ኤ. ሰላዮች ናቸው የመንግሥት አቋም አይቀበሉም የተቃዋሚዎች አባላት ናቸው በገንዘባቸውም ተቃዋሚዎችን ይደጉማሉ እና ሌሎች ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ የፈጥራ ክሶች እያመላለሰ ብዙዎችን የቤተ-ክርስትያን ሊቃውንት መምህራን የደብር አለቆች የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎችና ሰባኪያነ ወንጌል ለአላስፈላጊ ስደትና ህልፈተ ህይወት እየዳረጋቸው ይገኛል። 

ለዚህም ጭብጡ የኤርትራ መንግሥት በመጽሐፍ ቅዱስ አማኞችና አጠቃላይ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከባድ እርምጃ ወስዶ ሲያበቃ እነዚህ ፍጥጥ ብለው “ታማልዳለች” የሚል በመደለያ ሥም ይዘው ተደራጅተው እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ የሚጋልቡበት ምክንያት ምንድ ነው? የሚያምኑትም ሆነ የሚያስተምሩት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ወይ? ሌላ መጽሐፍ ቢኖራቸው ነው እንጂ መጽሐፉን አምነው የተቀበሉትና ያመኑትማ ስፍራቸው በድቅድቅ ጨለማ የመቃብር ስፍራ መሆኑን ዓለም የሚመሰክረው የአደባባይ ምሥጢር ነው። ሐዋርያዊትና አለም አቀፋዊትዋ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንም እንደሆነች ጉሉላትውና መሠረትዋ ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መምህራንዎችዋን የሚያውቁት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለተከታዮችዋም የምታስተምረው መጽሐፍ ይህን መጽሐፍ ነው። እነ “ማኅበረ-ቅዱሳን” (ታማልዳለች) ግን ከዚህ ሁሉ ዕዳ ነጻ ናቸው ይህም ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል የትርፍ ሰዓታቸው አገልግሎት ሆነዋል።

ይህ አሁን በአሥመራ ከተማ የሚገኘውን “የማኅበረ ቅዱሳን” ንዑስ ማዕከል ሀገርኛ ስሙ “ታማልዳለች” በመባል የሚታወቀው ማኅበር ከሀገሪቱ መንግሥት በቅንጅት እየሰራው ያለው ቤተ-ክርስቲያንን የማውደምና ሊቃውንቶችዋ የማሳደድ ሥራ ስልትዋ የአሥመራዎቹ ብቻ ሳትሆን በእኛ ላይም ሥራ ላይ የዋለች ስልት ለመሆንዋ አንድ የቅርብ ጊዜ ትዝታዬ ላጫውታችሁ። ተቀማጭነታቸው በምዕራቡ ዓለም ያደረጉ አባቶችና ሀገር ውስጥ የሚገኙት አባቶች አለመግባባትና ከዚህም አልፎ በውጪው ዓለም የሚገኙ አባቶች ራሳቸውን ችለው ሲኖዶስ ማቋቋማቸው ተከትሎ በሀገር ውስጥ የሚገኙ አባቶች ለጊዜውም ቢሆን የፈጠረባቸው ድንጋጤ ሥራ ፈቶ የሚለውና የሚጨብጠው አጥቶ የነበረ የሰይጣኑ ማኅበር “ማኅበረ-ቅዱሳን” ትልቅ የሥራ ዕድል የከፈተለት አጋጣሚ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ እየጠበቀ እንጀራውን የሚጋግር ዘመኑን የሚያራዝም ማኅበር ለተፈጠረለት የሥራ ዕድል ከመጠቀም ጊዜ አልፈጀም።

“ይህን ጉዳይ ለእኛ ተውት ብቻ እኛ በምናቀርብላችሁ “ችሮፖዛል” ተስማሙ ደጋፊዎቻቸው እነማን እንደሆኑና የት የት ቦታ እንዳሉ በቂ መረጃ አለን ቅዱስ አባታችን!” በማለት አንገቱን ያስገባ ይህን ዕድል ተጠቅሞ ካስፈጸማቸው አጀንዳዎቹ መካከል ከዚህ በፊት ክፉኛ የሚከታተላቸውና ምክንያት ያጣባቸው ደቀ-መዛሙርትን ይህን ዕድል ተጠቅሞ የሚሻውን መፈጸም ነበር። የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ-መዛሙርትም ሆኑ የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ-መዛሙርት ቀዳሚ የአጀንዳው ዒላማዎች ነበሩ። በተለይ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮለጅን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት የውጪ ሲኖዶስ ራሱን ችሎ መቋቋሙንና በይፋ ሊቃነጳጳሳት መሾሙን ዜና የተሰማ ዕለት አመሻሹ አጨብጫቢዎቹ ወደ ተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናትና ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ቅጽር ግቢ በማሰማራት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ ደቀ-መዛሙርት ቀንደኛ የውጪው ሲኖዶስ ደጋፊዎች እንደሆኑና በቅርቡ የሀገር ውስጡ ሲኖዶስ ተቃውሞው ሰለማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ክፉ የፈጠራ ወሬውን ነዛ።

ይህም (ወሬው) የብዙዎችን አባቶች ቀልብ ሊገዛም ችለዋል በቤተ-ክርስቲያኒትዋ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተቀመጡ ግለ ሰቦችም ክፉኛ በዚህ ተባራሪ ወሬ ተለክፈው ኮሌጁን ያለ አንዳች ተጨባጭ ምክንያት በዓይነ ቁራኛ መመልከት ተያያዙት በኮሌጁ ዙርያ ላይ የሚወሩ ማናቸውንም ዓይነት አሉባልታዎች  ተሰሚነት አገኙ ማህበሩም (“ማኅበረ-ቅዱሳን”) አስቀድሞ በጠረገው መንገድ ገብቶ ሥራው ጀመረ እንዳለው የውጪው ሲኖዶሱ አባላት መልቀም ሳይሆን ዕድሉን ተጠቅሞ በጥቁር መዝገቡ ላይ ያሰፈራቸውና ምክንያት ያጣባቸው ንጽሐን ደቀ-መዛሙርት መልቀም ተያያዘው 2ት ደቀመዛሙርት በግቢው ዘበኞች በደረሳቸው “የአባ” ጢሞቲዋስ (ቦ ጥሪት ዘአልቦ እውቀት) ደብዳቤ “በመናፍቅነት” ሥም እንዲባረሩ ተደረገ። በርከት ያሉ ደቀ-መዛሙርትም ያለ አንዳች ምክንያት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ወስደው የትምህርት ገበታቸው እንዲያጠናቅቁ ተደረገ 1998 ዓ.ም። በአሁን ሰዓት ሁለቱ በግፍ የተባረሩ የዲግሪ መርሀ ግብር ደቀ-መዛሙርት ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውና በማዕረግ መመረቃቸው ሰምቼአለሁ እጅግም ደስ ብሎኛል። ታድያ እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ምግባር ወይ መመሳሰል! በማለት አድንቀን እንለፈው ወይስ ራሱን እንላለን?    

ቀድሞም አሁንም ቢሆን በኤርትራ አብያተ-ክርስትያናት ለተፈጠርው ከፍትኛ ችግርና ለወደመው የቤ/ያን ንብረት፣ በእሥር እየተሰቃዩ ያሉ፣ እናት ሀገራቸውን ለቀው በስደት ምድር የሚገኙ፣ ከእምነታቸው የተነሳ ዛሬን ማየት ሳይታደሉ ቀርተው ደግሞ በሰማዕትነት የተለዩን የቅድስት ቤ/ያን ልጆችና ሊቃውንት መምህራን አባቶች ተጠያቂው ከደርግ ዘመን ጀምሮ “አጠቃላይ ጉባኤ” የሚል ሥም ቀጥሎም “ማኅበረ-ቅዱሳን” አሁን ደግሞ በአሥመርኛ “ታማልዳለች” የሚል በሚያማምሩ ሥሞች ገዳይ ማንነቱን እየሸፈነ የሚንቀሳቀስ የአራት ኪሎው አደገኛ “መንፈሳዊ” ቦዘኔ “ማኅበረ-ቅዱሳን” ለመሆኑ አጠር አጠር ያሉ ካገኘኅቸው ደረቅ መረጃዎች ከትግርኛ ወደ አማርኛ በመመለስ መረጃዊ ጽሑፌን አቅርቤ ልለያችሁ። 

እቲ ሓቂ እዚ ‘ዩ! ትርጉም “እውነቱ ይህ ነው” ሰቲት ጋዜጣ ዓርብ ታህሳስ 29/2000 ዓ.ም እ.አ.አ ገጽ.7  “ለጥቂት ዓመታት ወደኃላ መለስ ብለን የታሪክ መዛግብቶቻችን ስናገላብጥ “እኛ ብቻ ነን እውነተኞች ተዋህዶ!” ባዮች ኢትዮጵያውያን (አጠቃላይ ጉባኤ የአሁኑ “ማኅበረ-ቅዱሳን”) በደርግ ዘመነ መንግሥት ተነሥተው እናቶቻችን ወደ ቤተ-ክርስቲያን መምጣት እስኪያቆሙ ድረስ አማኙ ከቤተ-ክርስቲያን ለመነጠል ከባድ ሙከራ ተደርጎ እንደነበር እናስታውሳለን። ከተግባሮቻቸው መካከል አንዳንድ እንግለጽ “ቅዱስ ቦታ ነው ጫማችሁ ወደ ቅጽር ቤ/ያን አታስገቡ፣ እዚህ ተዉት ወርቅ ለሲነማ ቤት እንጂ ቤ/ያን ውስጥ አይገባም፣ ቀለበትሽ አውጪው፣ የለበሺው ነጠላ ለቤ/ያን አይበቃም ሂጂና ቀይረሺው ነይ ወ.ዘ.ተ” እያሉ ሲያስቸግሩ ይነበሩ ናቸው።

“በመቀጠልም እነዚህ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር የሌላቸው ኦርቶዶክስ ነን ባዮች ብዱኖች በቤተ-ክርስቲያን ላይም እንደሆነ ወንጌል በትግርኛ ሲነበብ በአንዳንድ የዋኅን እናቶች እንደ አንድ ትልቅ ሃይማኖትን የመለወጥ “ብለው ብለው ደግሞ ቄስ እግሌ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመሩ ይህማ የእኛ አይደለም” እያሉ በእነዚህ (ቅዱሳን መሳዮች ርኩሳን) አነሳሽነትና ትንኮሳ ብራና ላይ በግእዝ የተጻፈ ከልሆነ በስተቀረ ማተምያ ቤት የተጻፉ (የታተሙ) ቅዱሳት መጻህፍት መጻህፍት እንዳይደሉ፤ በቤተክርስቲያን (መጻህፍት) በግዕዝ ካልተበበቡ ለቤ/ያን እንደማይበቁ (የቤ/ያን እንዳይደሉ) የሚያንጸባርቁ ባህሪያት ታይተዋል እየታዩም ነው።“

ወደ ሀገራችን የማኅበሩ (“ማኅበረ-ቅዱሳን”) እኩይ ምግባር እንቅስቃሴ ልመልሳችሁ በተለይ የሀገራች ሰሜናዊ ክፍል የተመለከትን እንደሆነ ይህ አጋጣሚ “ማህበረ ቅዱሳን” በህዝቡ ልብ ያለአንዳች ጥርጣሬ ሰተት ብሎ እንዲገባ ረድቶታል። “ቤተ-ክርስቲያን ያለ ግዕዝ ቋንቋ መጻህፍቶችዋ በሌሎች ቋንቋ እየተተረጎሙ በቤተ-ክርስቲያን መነበብ የለባቸውም፤ እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥር ሁለቱ ይግባቡበት የነበረ ቋንቋ ግዕዝ ነው፤ በቤተ-ክርስቲያን መጻፍህት ከግዕዝ ውጭ በሌላ ቋንቋ ማንበብ ማለት ያለ ታቦት የመቀደስ ያህል ነው” እያለ ሲያስብለን የየዋኁን ህዝብ ልብ የሚያጠምዱ ቀልዶች በምእመናን ልብ እየዘራ  ነበር መረቡን የዘገጋ ይህን አልፎ ወንጌልም ሆነ መልዕክታት በአማርኛ ያነበበ እንደሆነ ሊቀጳጳሱም ሆነ ቄስ መጠሪያ ሥሙ “መናፍቅ” ነው። ክፉ ቀን ያዩ ዘንድ የሚያመልኩትና ዘመናቸውን ሁሉ በታማኝነት፣ በጽድቅ ያለ ነቀፋ ጉልበታቸው ለፈጣሪ እንዳስገዙ ያለፉ ብጹዕ አቡነ መርሀ ክርስቶስ የዚህ ሰለባ ነበሩ።

በመቀሌ ከተማ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት ለምሳሌ ያህል በጉግሳ ማሪያም ቅዱስት ማሪያም፣ አቡነ አረጋዊ፣ ደበረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ኪዳነ ምህረት ቤ/ያን በተለያዩ ጊዜያት በአንዳንድ አጋጣሚዎች (በሰርግ ጊዜና በትላልቅ በዓላት) የቤተ-ክርስቲያን መጻህፍት በአማርኛ ቋንቋ በመነበባቸው ብቻ በወቅቱ ያስነሱት ሰጣገባ እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ ጠባሳቸው አልተፋቀም። የዚህ ሁሉ መነሻም ራሱን ሳይደብቅ በመቀሌ ሀገረ ስብከት አከባቢ የምግብና መጠጥ ቤት ከፍቶ ንግዱን የሚያጧጥፍ የነፍሳት ደላላ ማኅበር “ማኅበረ ቅዱሳን” በቀጥታና በየአድባራቱ የሚገኙ የሰው መጋኛዎች አባላቱ በከፈተው ክስ ነበር። የዓዲ ግራት ከተማ አብያተ-ክርስቲያናትም በተመሳሳይ ስልት መታመሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ሌላም አለ የአሥመራው “ማኅበረ ቅዱስን” በሀገረ ኤርትራ የሚገኙት ያልተቀበሉት አብያተ-ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቶች ያሴረው ሴራ “ኮንቴነር ውስጥ የነበር ዕቃዎቻቸው ስንበትነው ኮንደም አግኝተንባቸዋል” (ኮንቴነሩ የርዕሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ያን ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ነው። አግኝተንባቸውዋል ባዮች ደግሞ በኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስትያን የተጠለሉ “የማኅበረ ቅዱሳን” አባላት ናቸው።) ጋዜጣው ይህን መሰረተ ቢስ ክስ አስመልክቶ እንደዳሰፈረው እንደሚከተለው ይነበባል “ኮንቴነሩ ሲከፈት እነማን ነበሩ? የቤተ-ክርስቲያኒትዋ ሰንበት ት/ቤት ንብረት የሆነውን ያላአንዳች ፈቃድ በጉልበት ሰብረው ገብተው ማውደም ያልተቸገሩ ኮንደም ኮንቴነር ውስጥ አስቀምጠህ ሥም ማጥፋት ያስቸግራል እንዴ?” ውድ አንባቢ ሆይ! መልስህ ምን ይሆን? ያስቸግራል ወይስ ምንችግር አለው! ይቻላል ይላሉ?

ዛሬ እንዲህ ራሱን የሚደብቅበት ሊያጣ የሰውን ክብር ጥላሸት መቀባትና ሥም ማጥፋት “ማኅበረ-ቅዱሳን” ብዙ ሳይለፉ በአቋራጭ ጎዳና በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጉልላት ላይ ያለ ጥያቄ የተከለው ሁነኛ ዘዴው ነበር። ኮንደምን በንጹሐን ሰዎች መጽሐፍ ላይ አስቀምጦ በመጽሐፍ ቅዱሳቸው ውስጥ ኮንደም አገኘንባቸው ይላል ወይ አይልም? ለሚለው በበኩሌ አይችልበትም እንጅ ሌላም ይላል ነው መልሴ። አንድ ከጥቂት ወራት በፊት አሜሪካን አገር በሚገኘው ሬድዮ ጣቢያው ማኅበረ ቅዱሳንንና አገልግሎቶቹን የሚያስተዋውቅ ልዩ የሬዲዮ ዝግጅት” በማለት የሰውን ክብርና ስም ያለ አንዳች ተጨባጭ መረጃ በአሉባልታ ማጥፋት መሆኑን ግልጽ መረጃ ነው። በአንድ በኩል “ማኅበረ ቅዱሳን” በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለውን ንቀት ነው የሚያመላክተው ያለ መረጃ የአንድን ድርጅት አልያም ግለ ሰብ ሥምን ማጥፋት በህግም ወንጀል ነው ለሰሚም ያስተዛዝባል። አስተዋይ ወይንም ደግሞ ሙሉ ሰው የለም የማለትም ያህል ነው።

የሬድዮ ዝግጅቱ የተጻፈውን መጽሐፍ አስመልክቶ ስለ መጽሐፉ አዘጋጅ (ስለእኔ) ማኅበሩ ሥሜን ለማደስ ይጠቅመኛ በማለት የአቅሙን ያክል ሞክረዋል። ምንም እንኳን የማኅበሩ ልሳኖች የማዳምጥበት ሰዓት በትልቁ ደግሞ በሥም ማጥፋት የሚያምን ስብእና ባይኖረኝም እግዚአብሔር ስለ ልጆቹ የሚሟገት አምላክ ነውና ይህን “የማኅበረ-ቅዱሳን” የዘንዶ አንደበት ሰምተው እንዳልሰሙ እንዲሁ የማያልፉ የቅድስት ቤ/ያን ልጆች አላሳጣንም።  ማኅበሩ (“ማኅበረ ቅዱሳን”) በሬድዮ ዝግጅቱ ላይ “ጥያቄዎቻችሁን እንመልሳለን” እንዲል ይህን መሰረት አድርገው ነዋሪነታቸው በዳላስ ቴክሳስ ያደረጉ ቁጥራቸው ከአስራ አምስት የማያንሱ ምእመናን ለማህበሩ ዋናው ቅጂ ለእኔ ደግሞ በአድራሻዬ በላኩት 2ኛ ቅጂ ባለ 9 ነጥብ ጥያቄ በተደጋጋሚ ጥያቅያቸውን አቅርበው ከማኅበሩ ዘንድ መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉና አሁንም ተስፋ ሳይቆርጡ እንደሚጠብቁ በመጠቆም ነበር የላኩልኝ።

መልስ እንሻለን በማለት አሜሪካ ለሚገኘው ለ“ማኅበረ ቅዱሳን” ልዩ የሬድዮ ዝግጅት የተላከ ጥያቄ ይህን ይመስላል፥

1. ይህ መጽሐፍ እምነቱን ጥሎ ወደ ሌሎች ጎራ በተቀላቀለ ሰው የተጻፈ ነውስትሉ እምነቱ ጥሎ ወደ ሌላ ጎራ ለመቀላቀሉ የምታቀርቡት የተቀረጸ ምስል ወይንም ደግሞ ፎቶ ግራፍ ማየት እንችላለን? ከዚህ በፊት ወደሌላ ጎራ ተቀላቀሉ ስትሉን እኛም አሜን ብለን የተቀበልናችሁ በምታቀርቡልን ተጨባጭ መረጃዎች ነበር፣ የመጽሐፉ አዘጋጅ የሆኑ / ሙሉጌታ ወልደገብሪኤል በየትኛው አደራሽ

2. “ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን የሚሳደብ ፀሐፊ የጻፈው ነው።”  እውን ተዋህዶ እምነታችን ሰድበው የጻፉት መጽሐፍ ወይም የሰሩት ስራ በተጨባጭ ልታቀርቡልን ትችላላችሁ? ተሳደቡ ከማለትስ እኛ አዎ! ተሳደቡ ለማለት እንድንችል ከተሳደቡ ስድቡን መናገር አይቀልም ነበር?

3.“የመጽሐፉ ደራሲ ራሱን ዲያቆን ብሎ የሚጠራእንደውመናፍቅለመሆኑ መረጃ አለን በማለት በድህረ ገጻችሁ አያይዛችሁ ያቀረባችሁት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ የአባ ጢሞቲዎስ ደብዳቤ የሚለው ለዲያቆን ሙሉጌታ ነው የሚለው አባባላችሁ በስህተት ነው ወይስ ልብ የሚል የለም ማለታችሁ ነው?

4.“እምነቱን በመለወጡ ምክንያት ከቤተ-ክርስቲያን የተባረረ ግለሰብ ነው።እምነቱን ሲለውጥ ኑዛዜውን የተቀበለው ማን ነበር?

5.“ግለሰቡ ከቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደተባረረ የሚያሳየው ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል።ደብዳቤው አድራሻ አድርጎ እንደጻፈው እኚህ ዲያቆን የተባረሩት ከኮሌጅ ነው ወይስ ከቤተ-ክርስትያን? ኮሌጅ አንድን ሰው ከቤተ-ክርስትያን መለየት የሚያስችል ስልጣን የተሰጠበት የቤተ-ክርስትያን አንቀጽ (ህገ ደንብ) ልጠቅሱልን ይችላሉ?

6.“ይህ ግለሰብ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሎጅ ከተባረረ በኋላ በሰራቸው ሌሎች ወንጀሎች ፖሊስ ሲፈልገው ወደ ኬንያ ሸሽቶ ጠፍቷል።ለምሳሌ ያህል ፖሊስ በወንጀል እንደሚፈልገው ማረጋገጫችሁ ምንድ ነው? የሰራውን ወንጀልስ ምንድን ነው? ከሰራቸው ወንጀሎች አንድ በመጥቀስ ልትገልጹልን ትችላችሁ? ለምንድነው የሸሸው ብላችሁ ግለሰቦችም ሆኑ ፖሊስን ስትጠይቁ ምን ወንጀል ሰራ ተብሎ ነበር የተነገራችሁ? ይህ ከሆነ ሰራው ተብሎ የተነገራችሁ ወንጀል ምንድ ነው? ባዩስ ማን ነው? የሰማችሁትን ልታካፍሉን ትችላላችሁ?

7.“ከዚያም ባሻገር ከማኀበረ ቅዱሳን ውጪ ስላለው እምነትና ስለሚጽፈው ፀረ ኦርቶዶክስ ጽሑፍ መናገር ነበረበት።አስቀድማችሁ የምታውቁና የሰማችሁ እንደው ስማችን አጠፋን እያላችሁ ያላችሁት እናንተው ናችሁ ጸሐፊው ከኦርቶዶክስ ውጪ ስላለቸው እምነት እና ስለ ጻፍቸው ጸረ አርቶዶክስ ጽህፎች ለማንበብ እንግዲህ እናንተን እየጠበቅን ነውና ልታስነብቡን ትችላላችሁ?

8.“ኦርቶዶክስን ከሚሳደብና ከሚያንቋሽሽነገር መደጋገም ሆነ እንጂ ደራሲው ቤተ-ክርስቲያናችን ተሳድበው የጻፉትን ጽሑፉም ሆነ ስብከት ካላቸው አቅርቡልን።

9.“በተለያዩ ቦታዎች ስለ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም ያለውን መዝለል አልነበረበትም።ሌላው ይቅር ፓትሪያሪኩን ሲሳደብ ወይንም ደግሞ ሲዘልፍ በአንድ ቦታ ያለውን ነገር ያስነብቡን (ያስደምጡን) እኛም አሜን ብለን እንቀበላችሁ፣ ያወገዛችሁትንም አብረን እናውግዛቸው።

እንግዲህ እነዚህ ጥያቄዎችን ወደ ሬድዮ ዝግጅት ክፍላችሁ ለመላክ የተገደድንበት ዋና ምክንያት በመግቢያችን ለመግለጽ እንደሞከርነው ማንኛውም ጥያቄአችሁ እንመልሳለን በማለት በገባችሁልን ቃል መሰረት ነው።  

“የተከበራችሁ አንባቢያን! በደርግ ዘመነ መንግሥት አንድ ወታደር የሲቪል ልብስ ልብሶ እህል ወደ ሚሸጥበት መጋዘን ይገባል “ይህ ጤፍ ጥሩ ነው? ለኩንታል ስንት ትለዋለህ? እያለ ጤፉ ላይ እጁን ልኮ ማገለባበጥ ጀመረ ከመዳበርያው እጁን በማውጣት ለጤፉ ባለቤት “ናስቲ ወንበዴማ እዚህ ነው ያለኸው እህል እያልክ ጥይት እያስገባህ ያለኸው” በማለት የክላሽ ጥይት አሳየው የእህሉ ባለቤት በማያውቀው ነገር ህይወቱ በድርጋውያን ስታልፍ ታይተዋል። ወታደሩም እንዳሰበው ያለ ገንዘብ ጤፍዋን ይዞ ይሄዳል። በሌላ ጊዜ የለመደች እጅ ጤፍ ለመውሰድ ጥይት በእህል መዳበሪያ ላይ ስታስቀምጥ ትያዛለች።” በማለት ባልወሉበት ለተከሰሱበት ጉዳይ በእውነተኛ ምሳሊያዊ አነጋገር መልስ ይሰጣሉ ተገፊዎቹ የርዕሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ያን ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች። አሁን ግን ዓለም የተገፊዎች ጩኸትና ኃዘን የምታስተናግድበትና የምታይበት ጊዜ ሳይሆን ገፊዎች የዘሩትን የሚያጭዱበት ሰዓት ነው።

የማኅበረ-ቅዱሳን” ፖለቲካዊና ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በኤርትራ አብያተ-ክርስቲያናት በሚል ርዕስ ለተከታታይ ሲቀርብ የነበረውን ጽሑፍ እዚህ ይገባደዳል

የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተ-ክርስትያናችን ይጠብቅ!

ጥበብ በዚህ አለ!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Diocese



 



 


ካብ ውሽጢ ኤርትራ ዝተረኽበ ንቤተ ክርስቲያን ተዋህዶ ንምቁጽጻር ብመንግስቲ ኤርትራ ክካየድ ዝጸንሐን ዘሎን ሽርሒ ዘቃልዕ ቪድዮ 



Support Tewahdo TV

Gofundme


Support Diocese

PayPal


ድኳን መጻሕፍቲ/Book Store


ጋዜጣ ፍኖተ ብርሃን፡ ልሣን

 ቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ


ስብከተ ወንጌል


ራድዮ ቃለ ኣዋዲ


መጻሕፍቲ - Books 


ጾምን በዓላትን


Diocese Churches

 

Radio Tewahdo

 Video - Youtube

TV Tewahdo

A Message from H.G. bishop Mekarios

መጸናንዒ ቃል ብብጹእ ኣቡነ መቃርዮስ

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተዋህዶ ብኸመይ

</div